ቤተክርስቲያኗ ለተፈናቃዮች 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት የቤት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች - ኢዜአ አማርኛ
ቤተክርስቲያኗ ለተፈናቃዮች 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት የቤት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች
ነቀምቴ ግንቦት 13/2011 የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በምዕራብ ኦሮሚያ አዋሳኝ በነበረው ግጭት ተፈናቅለው ለነበሩ ወገኖች ግምቱ 1ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ድጋፍ አደረገች።
የቤተክርስቲያኗ ማዕከላዊ ሲኖዶስየልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን ዳይሬክተር አቶ ተሰማ ጃለታ ድጋፉን ያደረገችው በክልሎቹ መካከል በተደረሰው እርቅ ወደ መኖሪያቸው ለተመለሱ ወገኖች ነው ፡፡
ድጋፉበምሥራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ ወደ ቀድሞ ቄያቸው ለተመለሱ ለቢፍቱ በሎና በረዳ ቀበሌዎች ለሚገኙ 450 አባወራዎች መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በድጋፉ ከተሰጡት ቁሳቁሶች መካከል 900 የብርድ ልብሶች፣900 ጂባዎች የወለል ምንጣፎች/፣ለመጠለያ የሚያገለግሉ 900 ሸራዎች፣900 የውሃ ጀሪካኖች እንደሚገኙበት ገልጸዋል፡፡
የቢፍቱ በሎ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር መልካሙ ኢታና በሰጡት አስተያየት ቤተክርስቲያኗ ያበረከተችላቸው የቤት ቁሳቁስ መልሶ ለመቋቋም በሚያደርጉት ጥረት እገዛ እንዳደረገላቸው ተናግረዋል፡፡
ሌላው የዚሁ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ተመስጌን ኢታና በበኩላቸው ድጋፉ ችግራቸውን አንዳቃለላቸው ተናግረዋል፡፡ለቤተ ክርስቲያኗም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የሳሲጋ ወረዳ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ኢትቻ በበኩላቸው ቤተክርስቲያኗ ከመንግሥት ጎን በመቆም ላደረገችው ድጋፍ በራሳቸውና በወረዳው ሕዝብ ስም ምሥጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡
ቤተ ክርስቲያኗ ቀደም ሲል ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ግምታቸው ሁለት ሚሊዮን ብር የሚገመት ፍራሾችና ብርድ ልብሶችን ድጋፍ ማድረጓ ይታወሳል ፡፡