የኢትዮጵያን  የለውጥ እርምጃዎች እደግፋለሁ -የአውሮፓ ህብረት

65
ግንቦት 29/2010 የኢትዮጵያ መንግሥት እየተገበራቸው ያሉ የለውጥ እርምጃዎችን እንደሚደግፍ የአውሮፓ ህብረት አስታወቀ፡፡ ህብረቱ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ማንሳቱን አድንቋል፡፡ የአዋጁ መነሳትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ የሚመሩት መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየወሰዳቸው ላሉ በጎ እርምጃዎች ቀጣይነት አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው ገልጿል። የኢፌዴሪ መንግስት በለውጥ ሂደቱ አካታች ማህበረሰብን ለመፍጠር የተለያዩ  ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝም ህብረቱ በመግለጫው ጠቅሷል። ህብረቱ የሀገሪቱ መንግስት በኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች እያደረጋቸው ያሉ የለውጥ ሂደቶችን ለመደገፍ ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጧል፡፡ ምንጭ፦eeas.europa.eu
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም