የአማራ ህዝብ ባህል ማዕከል በአዲስ አበባ እንዲገነባ ተጠየቀ

257

ግንቦት 10/2011 የአማራ ህዝብ ባህልና ታሪክ የሚያሳይ "የባህል ማዕከል" በአዲስ አበባ እንዲገነባ የክልሉ ተወላጅ ምሁራን ጠየቁ።

የአማራ ክልል ተወላጅ ምሁራንየተሳተፉበት በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ የተሳተፉት ሊቃን በየትኛውም  የአገሪቷ  አካባቢዎች  ለሚኖሩ የአማራ  ህዝብ ታሪኩንና ባህሉን የሚያሳይበት የባህል ማዕከል እንዲገነባ ጠይቀዋል።

ይህም ከየትኛውም አካባቢ ለሚመጡ እንግዶች የአማራን ባህልና ታሪክ ለማስተዋወቅ እንደሚያስችል አመልክተው፤ ማዕከሉም በአዲስ አበባ መገንባት እንዳለበት ነው የተጠቆመው።

ማዕከሉ የታሪክና የባህል ጥናትና ምርምሮች የሚደረጉበት ተቋም መሆን እንዳለበትም ጠያቂዎቹ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም