በጅማ ዞን የልምምድ አውሮፕላን ወድቆ አብራሪው የመቁሰል አደጋ ደረሰበት - ኢዜአ አማርኛ
በጅማ ዞን የልምምድ አውሮፕላን ወድቆ አብራሪው የመቁሰል አደጋ ደረሰበት
ግንቦት 9/2011 ንብረቱ የአቢሲኒያ ፍላይት ሰርቪስ የሆነ የልምምድ ሲሲና 172 አውሮፕላን በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን አሰንዳቦ አካባቢ ወድቆ በልምምድ ላይ የነበረው አብራሪ የመቁሰል አደጋ ደረሰበት።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለስልጣል የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንሙት ለማ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በልምምድ ላይ ያለው አውሮፕላን የወደቀው ዛሬ ጠዋት ከረፋዱ አራት ሰዓት ላይ ነው።
በአደጋው በስልጠና በረራ ልምምድ ላይ የነበረው ፓይለት የመቁሰል አደጋ እንደደረሰበትም ጠቅስዋል።
የትራንስፖርት ሚኒስቴር የአደጋውን መንስኤ የሚያጣራ የባለሙያዎች ቡድን ወደ ሥፍራው መላኩንም አስታውቀል።