ባንኩ ለመኖሪያ ቤት አግልግሎት ከወለድ ነጻ የዳያስፖራ የፋይናንስ አግልግሎት መስጠት ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
ባንኩ ለመኖሪያ ቤት አግልግሎት ከወለድ ነጻ የዳያስፖራ የፋይናንስ አግልግሎት መስጠት ጀመረ
ግንቦት 9/2011 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመኖሪያ ቤት አግልግሎት የሚውል ከወለድ ነጻ የዳያስፖራ የፋይናንስ አግልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ።
ባንኩ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ከወለድ ነጻ የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያችስል አሰራር ይፋ አድርጓል።
የባንኩ የጥራትና ቁጥጥር ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ እመቤት መለስ አዲሱ አገልግሎት ህዝበ ሙስሙን ጨምሮ ሌሎች ከወልድ ነጻ አግልግሎት የሚፈለጉ ዳያስፖራዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን የሚፈለጉ ዳያስፖራ ወዲዓ‘ህ የቁጠባ ሂሳብን በመጠቀም በትንሹ 20 በመቶ የሚሆነውን ገንዘብ በእንግሊዝ ፓውንድ፣ በአሜሪካን ዶላርና በዩሮ መቆጠብ ከቻሉ የአግልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ ተብሏል።
ይህም በዋናነት ግንባታቸው የተጠናቀቀና በጅምር ላይ ያሉ ቤቶችን ለመግዛት አመች ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል ተብሏል።
ለቤት መግዣ የሚውለውን ፋይናንስም እስከ 20 ዓመት ባለ የጊዜ ቆይታ ከፍለው መጨረስ የሚችሉ ይሆናል።
መስፈርቶችን የሚያሟሉ ዳያስፖራዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ወይም በሚኖሩበት ሀገር በሚገኝ ኤምባሲ በኩል የወዲዓ ‘ህ የቁጠባ ሂሳብ መክፈት ይችላሉ ሲል ባንኩ ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል።