ቀጥታ፡

በወላይታ ሶዶ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

ግንቦት 9/2011 ለውጡን በመደገፍ የልማት ጥያቄ የተነሳበት ሰላማዊ ሰልፍ በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

የሰልፉ ተሳታፊዎች ባሰሙት መፈክር  አሁን የተጀመረው ሃገራዊ ለውጥ በመደገፍ ሂደቱ በምንም መልኩ ሊደናቀፍ እንደማይገባም አመልክተዋል፡፡

ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነት ይረጋገጥ፣ የወላይታ ዞን  ክልል እንሁን ጥያቄ ይመለስ፣ ብሄርን መሰረት ያደረገ ጥቃትና መፈናቀል ይቁም የሚሉ መልእክቶችንም አስተላልፈዋል፡

በሰልፉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው፡፡

እስከ አራት ሰዓት እንደሚቆይ በተገለጸው ሰልፉ  የክልሉና የዞን አመራሮች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም