የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ጀመረ

52

ግንቦት 8/2011 የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ)  ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ።

ኮሚቴው ዛሬ በሚያካሂደው ስብሰባ በብሄራዊ ደህንነትና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያይ ተገልጿል።

ለውይይት በሚቀርብ ሰነድ ላይም ከተወያየ በኋላ ቀጣይ  አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎም ይጠበቃል።

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በአጭር ጊዜያት ውስጥ በተከታታይ እየተገናኘ ስራዎችን በጋራ እንዲገመግምና አቅጣጫዎችን እንዲያስቀምጥ መግባባት ላይ እንደደረሰ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ገልጾ ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም