የቤጂንግ አዲሱ አየር መንገድ የመጀመሪያውን የተሳካ የበረራ ሙከራ አድርጓል - ኢዜአ አማርኛ
የቤጂንግ አዲሱ አየር መንገድ የመጀመሪያውን የተሳካ የበረራ ሙከራ አድርጓል
ግንቦት 6/2011 አዲሱ የቤጂንግ ዳሲንግ አለም አቀፍ አየር ማረፈያ በአራት አውሮፕላኖች ተሳፋሪዎችን ይዞ የተሳካ የመጀመሪያ የበረራ ሙከራውን ማድረጉን ዥንዋ ዘግቧል።
ለሙከራ በረራው ተሳታፊ ከነበሩት አየር መንገዶች የቻይና ደቡባው አየር መንገድ፣ የቻይና ምስራቃዊ አየር መንገድ፣ የቻይና አየር መንገድ እና ዣማን አየር መንገድ ሞዴላቸው A380፣ A350-900፣ B747-8 እና B787-9 የሆኑ አውሮፕላኖችን በመላክ የተሳካ ሙከራ ማድረገ ችለዋል ።
የበረራው ሙከራ አዲስ የተገነባው የቻይና አየር መንገድ ዋና ትኩረቱን ከመሰረተ ልማት ግንባታ ወደ የኦፕሬሽን ዝግጅት ማዞሩን ያመላክታል ያሉት የቻይና የሲቪል አቪየሽን አስተዳደር ባለስልጣን የሆኑት ዋን ዣንግዶንግ ናቸው፡፡
አየር መንገዱ የተለያዩ የሙከራ በረራዎችን ካደረገ በኋላ እኤአ መስከረም 30/2019 በፊት ወደ ሙሉ ትግበራ ይገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ በዘገባው ተጠቅሷል።
አየር መንገዱ የተገነባው በቤጅንግ በደቡባው ክፍል 46 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ሲሆን በዋና ከተማዋ የሚገኘውን አለም አቀፍ አየር መንገድ የሚያጋጥመውን የመንገደኞች መጨናነቅ ለመቀነስ ታሳቢ በማድረግ ነው።
አየር መንገዱ ያረፈበት ቦታም ዋና ከተማዋን ከሚያዋስኑ ግዛቶች ዳሲግ እና ላግፋንግ ግዛቶች መካከል ሲሆን ከሂቤ ግዛት አቅራቢያ ነው።
አዲሱ አየር መንገድ በ2021 በዓመት 45ሚሊዩን መንገደኞችን በማስተናገድ በ2025 ደግሞ አገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል 72ሚሊዩን የሚደርሱ መንገደኞችን እንደሚያስተናግድ ይገመታል።