የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት አልበሺር በተቃውሞ ሰልፈኞች ግድያ ወንጀል ተከሰሱ - ኢዜአ አማርኛ
የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት አልበሺር በተቃውሞ ሰልፈኞች ግድያ ወንጀል ተከሰሱ
ግንቦት 6/2011የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሺር የተቃውሞ ሰልፈኞች ህጋዊ ያልሆነ እርምጃ እንዲወሰድባቸው በማዘዝና እንዲገደሉ በማድረግ ወንጀል መከሰሳቸውን የሀገሪቱ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ገልጿል።
አል በሺር ከህገወጥ ገንዘብ ዝውውርና ሽብርን በገንዘብ ከመደገፍ ጋር በተገናኙ ወንጀሎችም ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ተብሏል።
ሆኖም የተወሰኑ ሱዳናውያን አል በሺር ፍርድ ቤት ቀርበው እስካላየን ድረስ ስለተባሉት የወንጀል ክሶች አናምንም ብለዋል።
የቀድሞው የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር አል በሺር ከአንድ ወር በፊት በሀገሪቱ ወታደራዊ ኃይል ከስልጣን ወርደው 29 ዓመት የኖሩበትን ስልጣን አጥተዋል።
ሀገሪቱ አሁን በወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት እየተመራች ነው።
ምንጭ፦ቢቢሲ