ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር ተወያዩ

64

ግንቦት 6/2011 የኡጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ ኢንቴቤ ከተማ በሚገኘው ፅህፈት ቤታቸው ትናንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተቀብለው አነጋግረዋል።

ውይይታቸው በቀጣናዊ ትብብር እና በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ያተኮረ ነበር ።

በተለያዩ መስኮች ለረጅም ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ እና የዑጋንዳ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መግባባት ላይ መድረሳቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

ሁለቱ ሃገራት በቀጣናው  በሚስተዋሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይም የተወያዩ ሲሆን በቀጣይ በቀጣናው ትብብራቸውን ለማጥበቅ በሚችሉበት አግባብ ዙሪያ ተስማምተዋል።

በመጨረሻም ከኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተላከውን የትብብር መልዕክት ፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ እጅ ተቀብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም