ቀጥታ፡

ስሑል ሽሬ 1 ለ 0 ኢትዮጵያ ቡና አሸነፈ

ሽሬ ግንቦት 2 / 2011 በኢትየጵያ ፕሪሚዬር ሊግ 24ኛው ሳምንት ጨዋታ ዛሬ በሽሬ ስታዲዬም ጨዋታውን ያደረገው ስሑል ሽሬ ኢትዮጵያ ቡናን አንድ ለባዶ አሸነፈ።

በኢትየጵያ ፕሪሚዬር ሊግ 24ኛው ሳምንት ጨዋታ ዛሬ በሽሬ ስታዲዬም ጨዋታውን ያደረገው ስሑል ሽሬ ኢትዮጵያ ቡናን አንድ ለባዶ አሸነፈ።

ስሑል ሽሬ ኢትዮጵያ ቡናን አንድ ለባዶ በማሸነፍ ነጥቡን ወደ 22 ከፍ አደረገ።

ኢትዮጵያ ቡና በ33 ነጥብ ለመቆየት ተገዷል።

ስሑል ሽሬ ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት ኢትዮጵያ ቡና ወደ መሪዎቹ ለመጠጋት ያደረጉትን እልህ አስጨራሽ ጨዋታ የሽሬ ከተማ ስፖርት አፍቃሪ ቁጭ ብድግ ያደረገ ቀልብ ሳቢ ፉክክር ነበር።

በሁለተኛው አጋማሽ ስሑል ሽሬዎች ተጠናክረው በመግባት በ57ኛው ደቂቃ ሳፊ ፎፎና ያስቆጠራት ግብ በአሸናፊነት ለመውጣት አስችላዋለች።

የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ዋና አስልጣኝ ገዛኽኝ ከተማ ጨዋታውን አስመልክተው ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት “ቡድናችን ባሳየው ጥሩ ጨዋታ ሊሸነፍ አይገባውም ነበር” ሲሉ በውጤቱ የተሰማቸውን ቁጭት አንጸባርቀዋል።

በጨዋታው ስሑል ሽሬዎች ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት እልህ አስጨራሽ ጨዋታ በማድረግ ሙሉ ሦስት ነጥብ ይዘው ለመውጣት አስችሏቸዋል።

የስሑል ሽሬ ክለብ  ዋና አስልጣኝ ሳምሶን አየለ በበኩላቸው ''በሜዳችን በደጋፊያችን ፊት አሽንፈን ለመውጣት ያደረግነውን እልህ አስጨራሽ ጨዋታ በድል አጠናቅቀናል'' ሲሉ ደስታቸውን ገልጸዋል።

ቀሪ ጨዋታዎች በማሸነፍም በሊጉ ለመቆየት ጥረት እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

በሺህዎች የሚቆጠሩ የሽሬ እንዳስላሴ ከተማ የስፖርት አፍቃሪዎች ክለባቸውን አበረታተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግን መቀሌ ሰባ እንደርታ በ48 ነጥብ በመምራት ላይ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም