ቀጥታ፡

ኢዜማ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን የድርጅት መሪ፣ አቶ የሺዋስ አሰፋን ሊቀ መንበር አድርጎ መረጠ

አዲስ አበባ ግንቦት 2/2011 የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን የድርጅቱ መሪ፣ አቶ የሺዋስ አሰፋን ሊቀ መንበር አድርጎ መረጠ።

'የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በሚል የሰባት ፓለቲካ ድርጅቶችን አዋህዶ የተመሰረተው ፓርቲ ከትናንት ጀምሮ ባካሄደው የምስረታ ጉባኤ ዛሬ የፓርቲ አመራሮችን መርጧል።

በዚህም ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋን በድርጅት መሪነት፣ አቶ አንዷለም አራጌን በምክትልነት፣ አቶ የሺዋስ አሰፋን የፓርቲው ሊቀ መንበር፣ ዶክተር ጫኔ ከበደን ደግሞ ምክትል ሊቀ መንበር አድረጎ መርጧል።

በምርጫ ሂደቱም ፕሮፌሰር ብርሃኑ በ912 ድምፅ እንዲሁም አቶ የሺዋስ ደግሞ በ722 ድምጽ መመረጣቸው ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም