የአውሮፓ አገራት 25 ከመቶ በጀታቸው ለአየር ንብረት ለውጥ ስራዎች እንዲያውሉ ተጠየቀ - ኢዜአ አማርኛ
የአውሮፓ አገራት 25 ከመቶ በጀታቸው ለአየር ንብረት ለውጥ ስራዎች እንዲያውሉ ተጠየቀ
ሚያዝያ 30/2011 የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት 25 መቶ ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እንዲውል ጠየቁ፡፡
ስምንት የአውሮፓ የህብረቱ አባል ሃገራት 25 ከመቶ በጀታቸው ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖን ለመከላከል እንዲመድቡ ለህብረቱ ጥያቄ አቀረቡ፡፡
አገራቱ በጋራ ባወጡት መግልጫ የአውሮፓ ህብረት እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2050 የተበከለ አየር ልቀትን ዜሮ ለማድረስ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
የጋራ መግለጫውን ያወጡት ፈረንሳይ፣ቤልጂየም፣ ዴንማርክ፣ ሉክሰምበርግ፣ ኔዘርላንድ፣ ፖርቹጋል፣ ስፔን እና ስዊድን ናቸው፡፡
አገራቱ ጥያቄውን ያቀረቡት የአውሮፓ መሪዎች በሮማኒያ በህብረቱ የቀጣይ 5ዓመታት ስትራተጂ ዙሪያ እየመከሩ ባሉበት ወቅት ነው፡፡
አገራቱ እጅ ለእጅ ተያይዘን በመበልፀግ ለሌሎች አገራት አርአያ ልንሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ሆኖም 28 አገራት ያቀፈ የአውሮፓ ህብረት እንደ ጀርመን የመሳሰሉት ጠንካራ አገራት በጥያቄው ላይ ባለመካተታቸው ሁኔታውን ከባድ ያደርገዋል ተብሏል፡፡
በአህጉሩ የሚገኙ ወጣቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የከባቢ አየር ብክለትን የሚያደርሰው ተፅእኖ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ እየጠየቁ ነው የሚለው የጋራ መግለጫው መንግስታትም እንድ ህብረቱ ለአየር ንብረት ለውጥ ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ አስታውሰዋል፡፡
ለዚህም የአውሮፓ አገራት ከአጠቃላይ በጀታቸው 25 ከመቶ ለአየር ንብረት ለውጥ ተፅእኖ መከለከያ ስራዎች ሊበጅቱ እንደሚገባ ነው የተጠየቀው፡፡
ስምንቱ የአውሮፓ ህብረት አገራት ህብረቱ በሚቀጥለው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ ላይ በ2050 የበካይ ጋዝ ልቀትን ወደ ዜሮ ለማድረስ የሚያስችለው ፖሊሲ ይፋ እንዲያደርጉ እና የፓሪስ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
የመረጃው የቢቢሲ ነው