ፌዴሬሽኑ በዚህ ወር በአፋር ክልል ሕይወቱ ላለፈውና ለተጎዱ ስፖርተኞች የሞራል ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
ፌዴሬሽኑ በዚህ ወር በአፋር ክልል ሕይወቱ ላለፈውና ለተጎዱ ስፖርተኞች የሞራል ድጋፍ አደረገ
መቀሌሚያዝያ 29/2011 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአፋር ክልል ሕይወቱ ላለፈውና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ስፖርተኞች የሞራል ድጋፍ ዛሬ አደረገ።
የሟች ቤተሰቦችና የክለቡ አባላት በበኩላቸው በተደረገው ድጋፍ መኩራታቸውን ገልጸዋል።
ፌዴሬሽኑ ድጋፉን ያደረገው ወደ ትግራይ ክልል ሲጓዙ ጉዳት ለደረሰባቸው የዋልታ እግር ኳስ ክለብ አባላት ነው።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጁራ በአደጋው ሕይወቱ ላለፈው አማኑኤል ብርሃነ ቤተሰብ 50ሺህ ብር ፤ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው አምስት የክለቡ አባላት በነፍስ ወከፍ 25 ሺህ ብር አበርክተዋል።
ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ወቅት የሟች ቤተሰቦችና ጥቃት የደረሰባቸው ስፖርተኞች እንዲጽናኑ ጠይቀዋል።
ክለቡ በተፈጠረው ችግር ሳይንበረከክ እንዲጠናከርም አቶ ኢሳያስ አሳስበዋል።
የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር መኮንን ካህሳይ በበኩላቸው ፌዴሬሽኑ አደጋው ከተፈፀመ ጀምሮ እስካሁን እያደረገ ያለው ክትትልና ድጋፍ እንዳረካቸው ገልጸዋል።
ክልሎች ፀረ ሰላም ኃይሎች ለመያዝ በሚደረገው እንቅስቃሴ ተቀናጅተው እንዲሰሩም ጠይቀዋል።
የሟች አማኑኤል ቤተሰቦችና የአካል ጉዳት የደረሰባቸው የክለቡ አባላት በተደረገው ድጋፍ መኩራታቸውን ተናግረዋል።
በክለቡ አባላት ላይ በአፋር ክልል ገዋኔ ወረዳ እንድፍኦ ቀበሌ ማንነታቸው ባልታቁ ሰዎች ጉዳት የደረሰው ባለፈው ሣምንት ነበር።