በኬንያ ኢትዮጵያውያን ለትረስት ፈንድ 20 ሺህ ዶላር አዋጡ

127

ሚያዝያ 29/2011 በኬንያ ኢትዮጵያውያን ለትረስት ፈንድ 20 ሺህ ዶላር ማዋጣታቸውን በኬንያ የኢፌዲሪ ኢምባሲ አስታወቀ።

በኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልድ ኢትዮጵያውያን በጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ለተጀመረው የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ነው 20 ሺህ ዶላር ማወጣት የቻሉት።

ኢትዮጵያውያኑ ሚያዚያ 12 ቀን 2011 ዓ.ም ባደረጉት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም 8 ሺህ ዶላር በአንድ ቀን አዋጥተዋል።

ከዚህ በፊትም በናይሮቢ የሚገኙ በተለይም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን ከ11 ሺህ ዶላር በላይ በቀጥታ ለዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ገቢ አድረገዋል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲም በናይሮቢ እና አካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እያደረጉ ያለውን አስተዋጽኦ የበለጠ ለማስፋት እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም