በስፖርቱ ውድድር ላይ ትኩረት ያደረገውን አሰራር መቀየር እንደሚገባ የስፖርት ምሁራን ገለጹ። - ኢዜአ አማርኛ
በስፖርቱ ውድድር ላይ ትኩረት ያደረገውን አሰራር መቀየር እንደሚገባ የስፖርት ምሁራን ገለጹ።
በስፖርት ውድድሮችላይትኩረት ባደረጉ አሰራሮችን መቀየር እንደሚገባ የስፖርት ምሁራን ገለጹ።
1990 ዓ.ም በወጣው የአገር አቀፍ የስፖርት ፖሊሲው ላይ በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎቹ ሁሉንም ዜጋ ባሳተፈ መልኩ መካሄድ እንደሚገባው ያስቀምጣል ።
ይህም በአካል የጠነከረና በአእምሮ ንቁና ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠርና በርካታ ተወዳዳሪ ስፖርተኞችን ለመፍራት እንደሚጠቅም ነው የሚያስቀምጠው ።
ይሁን እንጂ ፖሊሲው በአግባቡ እየተተገበረ አይደለም የሚሉ ትችቶች ይቀርቡበታል።
ይህም በዋናነት የሚመለከታቸው የመስኩ ተቋማት በቅንጅት ያለመስራት ችግር እንደሆነ ነው የዘርፉ ምሁራን የሚናገሩት።
በኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ የስፖርት መምህር ኢንስትራክተር የማነህ ጎሳዬ አሁን ላይ በፖሊሲ ደረጃ ህዝቡን በስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲሳተፍ ለማድረግ የተቀመጠ ነገር ቢኖርም የፖሊሲው አተገባበር ላይ ግን ሰፊ ክፍተት እንዳለበት ነው የተናገሩት ።
የወጣውን ፖሊሲ በማስፈፅም በኩል ፌዴሬሽኖች፣ ክለቦችና ከፌደራል ጀምሮ በዞን በወረዳና በቀበሌ ደረጃ ያሉ አስፈጻሚ አካላት አምነውበት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
ይህን ለማከናውን የተለያዩ ተቋማትን የቅንጅት ስራ የሚጠይቅ እንጂ የአንድና የሁለት ተቋማት ብቻ ስራ እንዳልሆነም ገልጸዋል።
ይህን የሚቆጠጣሩ አካለትም ክትትል ማድረግና አፈጻጸሙን በየጊዜው እየገመገሙ መሄድ ይገባቸዋል ብለዋል።
በኮተቤ ሜትሮፖሎታን ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር ወገኔ ዋልታንጉስ በበኩላቸው ፖሊሲውን ለማስፈፀም ክፍተት ከፈጠሩት ችግሮች መካከል የማዘውተሪያ ቦታዎች በሰፊው አለመሰራታቸው ነው ይላሉ።
አሁን ባለው ሁኔታ የተሻለ የማዘውተሪያ ቦታ ያለው በትምህርት ቤቶች አካባቢ ቢሆንም አብዛኞቹ ግን ለህብረተሰቡ ክፍት እንዳልሆኑ ነው የሚናገሩት።
የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ ዜጎች የአካል እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ከሚመከሩባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ የእግር ጉዞ ማድረግ ሲሆን በኢትዮጵያ ግን አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች የሀገሪቷ አካባቢዎችም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ አመቺ አለመሆናቸውን ይናገራሉ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የስፖርት ባለሙያ ዶክተር ዘሩ በቀለም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀመጡና ዜጎች በስፖርታዊ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉ የማድረግ መብቶችን የፈረመች ቢሆንም በአግባቡ እየተተገበሩ እንዳልሆኑ ነው ያብራሩት።
ይህን ችግር ለመፍታትም በተለይም በትምህርት ቤቶች አካባቢ ከፍተኛ ትኩርት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ይህንም ለማድረግ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የትምህርት ሚኒስትርና የጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ሌሎች መሰል ተቋማት በጋር ሆነው በቅንጅት መስራት ይገባቸዋል ብለዋል
ዜጎች አካላዊ እንቅስቃሴን አዘውትረው ካላደረጉ እንደ ሀገር ዘርፈ ብዙ የሆነ የጤናና የኢኮኖሚ ችግሮች እንደሚያስከትል ነው ምሁራኑ ያሳሰቡ