የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ሞት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ሞት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ
አዲስ አበባ ሚያዝያ 20/2011 የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ሞት የተሰማውን ሀዘን ገለጸ
ሚኒስቴሩ በመግለጫው በፕሬዝዳንቱ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለፅ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ተመኝቷል።
በተያያዘ ዜና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልእክተኛ አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸዋል።
ዶክተር ነጋሶ ከ1987 ዓ.ም ጀምሮ የኢፌዲሪ መንግስት ርእሰ ብሄር ሆነው በመሾም ለ7 ተከታታይ ዓመታት በፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል።
በ1997 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫም በኦሮሚያ ክልል ደንቢ ዶሎ በግላቸው ተወዳድረው ፓርላማ መግባታቸው ይታወሳል።
ከወጣትነታቸው ጀምረው በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርዓት እውን እንዲሆን ጉልህ ተሳትፎም ነበራቸው።
ዶክተር ነጋሶ በጀርመን ሀገር ህክምና ሲከታተሉ ቆይተው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የተነገረው በትናንትናው እለት ነበር።