ቀጥታ፡

የኢየሱስ ክርስቶስ መሰዋትነት ያለምንም ልዩነት ለሁሉም ሰው ልጆች መሆኑን በማሰብ በፍቅር አንድ ላይ መኖር ያስፈልጋል - ምዕመናን

ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያሳየው ፍቅርና የከፈለው መስዋዕትነት ያለምንም ልዩነት ለሁሉም ሰው ልጆች መሆኑን በማሰብ በፍቅርና በመተሳሰብ መኖር እንደሚገባ የስቅለት በዓልን ለማክበር የተገኙ ምዕመናን ተናገሩ። 

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክስቲያን ተገኝተው የስቅለት በዓልን ሲያከብሩ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ የሰው ልጆች በመተሳሰብ ና በፍቅር ተግባብተው መኖር አለባቸው።

የኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያሳየው ፍቅርና የከፈለው መስዋዕትነት ያለምንም ልዩነት ለሁሉም ሰው ልጆች መሆኑን በማሰብ በፍቅርና በመተሳሰብ አንድ ላይ መኖር እንደሚገባ ምዕመናኑ ተናግረዋል።

''የህዝብን አንድነት ከሚከፋፍሉ ድርጊቶች በመቆጠብ ማህበረሰቡ ትኩረቱን ለአገሪቱ ዕድገት የሚጠቅሙ የልማት ስራዎች ላይ ማድረግ ይገባል'' ብለዋል።

ምዕመናኑ ከክርስቶስ ፍቅር በመማር አንዱ ለሌላው በማሰብ በመተሳሰብ መኖር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከሞት ለማዳን የተሰቀለው ለመላው የሰው ልጅ በመሆኑ መከፋፈል ጥላቻ ውስጥ መግባት ሳይኖር በመተባበር በሰላም መኖር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ከአስተያየት ሰጭዎች መካከል  አቶ አዱኛ ላቀ   ፈጣሪያችን ለእኛ ለሰው ልጆች  የሰጠውን ፍቅር በማየት ፣ ከእሱ ተምረን እርስ በእርሳችን  ተፈቃቅርን   በመተሳሰብ መኖር ይገባናል ብሏል፡፡

ወጣት ሞገስ  ጌታቸው በበኩሉ   ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ   መልካም   ስራዎች   እንደ  አርያ  በመውሰድ   ከመጥፎ ተግባራት  መራቅ እንደሚገባ አመላክቷል፡፡

የሀይማኖት መሪዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና ሌሌች ተደማጭነት ያላቸው ሰዎች በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በፍቅር መኖርና መከባባርና ለማጠናከር ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸውም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም