በነጌሌ ከተማ ደጋፊ ለሌላቸው ዜጎች ለትንሳዔ በዓል የ200 ሺህ ብር ግምት ያለው ድጋፍ ተደረገ - ኢዜአ አማርኛ
በነጌሌ ከተማ ደጋፊ ለሌላቸው ዜጎች ለትንሳዔ በዓል የ200 ሺህ ብር ግምት ያለው ድጋፍ ተደረገ
ነጌሌ ሚያዝያ 18/2011በኦሮሚያ ነጌሌ ቦረና ከተማ ጧሪና ደጋፊ ለሌላቸው ወገኖች ለትንሳዔ በዓል መዋያ ከ200ሺህ ብር ግምት ያለው ድጋፍ ተደረገ።
ከከተማው የመንግሥት ሠራተኞችና በጎ ፈቃደኞች የተሰባሰበውን ድጋፍ ለ200 ወገኖች ተሰጥቷል።
ከተሰጡትም መካከል የቤት ውስጥ ማብሰያ ቁሳቁስ፣ 500 ሊትር የምግብ ዘይትና 20 ዶሮዎች ይገኙበታል፡፡
የከተማው ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሞሉ ኪቶ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት
በመረዳዳትና በመተሳሰብ ማህበራዊ ችግሮቻችንና ግዴታዎቻችን መወጣት ይገባል፡፡
ድጋፍ ከተደረገላቸው መካከል አቶ አሎ ቦነያ ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው፣ ድጋፉ የመረዳዳት ባህል ቀጣይነትን አመላካች ነው ብለዋል
ዜጎች ለሰላም፣ ለአብሮነትና ለመተባበር በጋራ መሥራት እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል፡፡