ቀጥታ፡

በሐረር የበዓል ገበያ የዋጋ ጭማሪ ታይቶበታል

ሐረር ሚያዝያ 18 ቀን 2011 በሐረር ከተማ የትንሳዔ በዓል ግብይት የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን ሻጮችና ሸማቾች ገለጹ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋዜጠኛ ያነጋገራቸው ተገበያዮች እንዳመለከቱት የበዓሉ ግብይት ካለፉት ዓመታት ጭማሪ ታይቶበታል።

ጭማሪው በተለይ ከዘንድሮው የገና በዓል ያለው ልዩነት ከ8ሺህ እስከ 10ሺ ብር እንደሚደርስም ገልጸዋል።

በዚህም ትልቅ ሰንጋ በሬ እስከ 50ሺህ ብር፣መካከለኛው ደግሞ ከ40 እስከ 45 ሺህ ብር እየተሸጠ ነው ።

እንዲሁም አንድ መሲና እስከ 25 ሺህ እስከ 30 ሺህ ብር በመሸጥ ላይ ናት።

አንድ ሙክት ፍየል 5ሺ 500ብር ሲያወጣ፣ መካከለኛው ደግሞ 4 ሺህ ብር እየተሸጠ መሆኑንም ጋዜጠኛው ተመልክቷል።

ትልቅ ወንድ ዶሮ 250ብር  ሲሸጥ ሴት ዶሮ 70 ብር  በመሸጥ ላይ ነው።

አንድ ኪሎ ለጋ ቅቤ 300 ብር፣ መካከለኛው 290 ብር ነው።የአንድ እንቁላል መሸጫ ዋጋም  አምስት ብር  ሆኗል።

አንድ ኪሎ ቀይ ሽንኩርት 22 ብር  ሲያወጣ፣ነጭ ሽንኩርት በኪሎ 80 ብር እየተሸጠ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም