ቀጥታ፡

በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ አንድ ሄሊኮፕተር ድንገተኛ ችግር ገጥሞት ወድቋል

አዲስ አበባ ሚያዚያ 18/2011 ንብረትነቱ የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የሆነ ሄሊኮፕተር ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተነስቶ በመብረር ላይ እያለ ባጋጠመው ድንገተኛ ችግር ቡልቡላ አካባቢ መውደቁ ተነገረ።

ንብረትነቱ የትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ የሆነ ሄሊኮፕተር ከሁለት አብራሪዎቹ ጋር አምስት መንገደኞችን አሳፍሮ ከቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተነስቶ በመብረር ላይ እያለ በገጠመው ድንገተኛ ችግር ቡልቡላ አካባቢ መውደቁን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ገልጿል።

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኮሎኔል ወሰንየለህ ሁነኛው ለኢዜአ እንደገለጹት የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ቢሆንም በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ግን የለም።

ትራንስ ኔሽን ኤርዌይስ በሚድሮክ ቴክኖሌጂ ግሩፕ ሥር የሚተዳደር ሲሆን በኢትዮጵያ ከሚገኙ የግል አየርመንገዶች መካከል አንዱ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም