የፀሎተ ሐሙስ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች ተከበረ - ኢዜአ አማርኛ
የፀሎተ ሐሙስ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች ተከበረ
አዲስ አበባ ሚያዝያ 17/2011 ህዝበ ክርስቲያኑ የሰላም ምልክት የሆነውን ትህትና በዕለት ተዕለት ህይወቱ ሊተገብረው እንደሚገባ ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ማቲያስ አስገነዘቡ።
እየሱስ ክርስቶስ ህፅበተ እግር ያደረገበትየፀሎተ ሀሙስ በዓል ዛሬ በቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ሃይማኖታዊ ስነ-ስርዓት ተከብሯል።
በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እንደገለጹት፤ የሃይማኖቱ ተከታዮች ክርስቶስ ለሰው ልጆች ያሳየውን ትህትናና ፍቅር እርስ በእርስ በመዋደድ በዕለት ተእለት ኑሯቸው መተግበር ይገባቸዋል።
ህዝበ ክርስቲያኑ ፈጣሪው ያስተማረውን ትህትና ወደ ራሱ ህይወት በመቀየር የበላዩን ብቻ ሳይሆን የበታቹንም በማክበርና በመታዘዘ መልካም ባህሪን መያዝ እንደሚገባው ነው ያሳሰቡት።
በሰሞነ ህማማት ህዝበ ክርስቲያኑ የሚያሳየ መልካምነት፣ትህትናና ፍቅር በህይወት ዘመኑ በሙሉ ሊለየው እንደማይገባም አቡነ ማቲያስ መክረዋል።
እየሱስ ክርስቶስ በጸለተ ሐሙስ የሃዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ በማጠብ ትህትናንና ታዛዥነት ያስተማረበት ነው።
አቡነ ማቲያስ የጳጳሳቱን እግር፣ ጳጳሳቱ ቆሞሳቱና ካህናቱ ደግሞ የምዕመናኑን እግር በማጠብ ሃይማኖታዊ ስርዓቱን ፈጽመዋል።