የአማራና የኦሮሞ ህዝብ አንድነት በደም የተሳሰረ ነው-የህዝብ ለህዝብ ውይይት ተሳታፊዎች - ኢዜአ አማርኛ
የአማራና የኦሮሞ ህዝብ አንድነት በደም የተሳሰረ ነው-የህዝብ ለህዝብ ውይይት ተሳታፊዎች
ሚያዝያ 15/2011 አማራና ኦሮሞ በታሪክ ፣ በጋብቻና በደም የተዋሃደ ህዝብ መሆኑን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ ተሳታፊዎች ተናገሩ። ከሰሞኑ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በተደረገው የአማራና ኦሮሞ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ ከሁለቱም ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ እንግዶች ታድመው ነበር። ኢዜአ ከተሳታፊዎች መካከል በሁለቱ ህዝቦች ላይ ስላላቸው ምልከታ አነጋግሯቸዋል። አማራና ኦሮሞ በታሪክ፣ በጋብቻና በደም የተዋሃደ ህዝብ መሆኑን ገልጸው፤ ሊሂቃኑ ግን በህዝቡልክአንድነትእንደሚጎላቸውያወሱትተሳታፊዎቹወደ ህሌናቸው እንዲመለሱ፣ ወጣቶችም በርጋታ ለውጡን እንዲያካሂዱ መልእክት አስተላልፈዋል'። ከተሳታፊዎች መከካከለል ከአርሲ የመጡት አቶ ቁፋ ጎቤ "አማራ ፣ ኦሮሞ ማለት የለም ስንፈጠረም በአምሳሉ ፈጥሮናል። አሁንም ቢሆን አማራ ኦሮሞ ወተትና ቅቤ ነው ፣ አንለያየም። የሚያለያየን የለም ፤ 150 ዓመት ወንበር የለመዱ የት እንቀመጥ ያሉ ፣ የሰውን ደም የጨረሱ፣ እነዚህ ናቸው መርፌ የሚያስወጉን እንጂ እኛ አሁንም ቢሆን ነገም ዛሬም ከአማራ የሚለየን ነገር የለም። እኛ የምንፈልገው ሰላም ነው፤ እድገት ነው፤ ልማት ነው፤ መቻቻል ነው፣ እኩልነት ነው።" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የአምቦ ነዋሪየሆኑትወይዘሮታሪኬክፍሌበበኩላቸው"አዲሲቷን ኢትዮጵያን ለመመስረት እንድንችል ያለፈውን ታሪክ እንድንተወው አዳፋ የሆነውን ታሪክ እንድንተወው፣ መልካሙን ነገር እንድናስቀጥል ምሁራን፣ ሊሂቃን በጣም ትልቅ ስራ መስራትና ማረም አለባቸው። ስህተት ሲመጣ ማረም አለባቸው። የሚታተሙ መጽሐፎች፣ የሚጻፉ ታሪኮች መጠናት አለባችው። ወደ ህዝቡ ሲወርዱ ያለው ነገርና ሰው እያደረገ ያለው ነገር ያደናግራል፤ የሚሰማውና የተጻፈው ነገር አንድ አይደለም። እና እንደዚህ አይነት ነገሮች ላይ ቢሰራ ብዬ አስባለሁ።" ብለዋል፡፡ ከደጀንእንደመጡየሚናገሩትአቶበልስአበበ በበኩላቸው "ኦሮሞ አማራ ፊት ላይ ሲጀመር የነበረው ህዝብ በደም፣ በጋብቻ በተለያዩ ነገሮች የሚገናኝ የሁለት አካል ህዝብ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን አሁን ባለንበት ሰዓት ላይ የፖለቲካ ምህዳር እየሰፋ በመጣ ቁጥር አንዳንድ ጥቅማቸው የተነካባቸው አካላት የአብሮነትን ህልውና ለማጥፋተ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን ወጣቱ አርዓያ ሆኖ ከተለያዩ አመራሮች፤ ከአማራ ኦሮሞ የተውጣጡ ምሁራኖች ደግፈን የለውጡ አርዓያ ሆነን እጅና ጓንት ሆነን ወደፊት ጠንክረን መስራት አለብን።" ነው ያሉት፡፡ የአምቦ ነዋሪው አቶተስፋዬ ዳባም "በጀግንነትም፣ በብዛትም፣ በሃብትም፣ በምንም የሚጣጣም ህዝብ ነው ይሄ ህዝብ። የዚህ ህዘብ አንድ መሆን የጠላት ከፍተኛ ስጋት ነው። የዚህ ህዝብን አንድ አለመሆን ደግሞ መበታተን ነው። መበታተን ደግሞ አቅም ማሳጣት ነው። እኔ የኦሮሞ ምሁራንም ሆኑ የአማራ ምሁራን ለወደፊት ማድረግ የሚገባቸው እኔ እበልጣለሁ፣ እኔ ነኝ ኢትዮጵያዊ ማለቱን ትቶ አባቶቻችን፣ አያቶቻችን ለከፈሉላት በአጥንታቸውና በደማቸው ያጠሯትን አገር በአንድነት ለመገንባት አንድነቱን አጠናክሮ መስራት አለባቸው። መለያየት አቅም ማጣት ነው። መለያየት ለጠላት መንገድ መክፈት ነው።