በሦስተኛው ዙር ብሔራዊ የክለቦች የቦክስ ውድድር ማራቶን ስፖርት በወንዶች አሸናፊ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
በሦስተኛው ዙር ብሔራዊ የክለቦች የቦክስ ውድድር ማራቶን ስፖርት በወንዶች አሸናፊ ሆነ
ደሴ ሚያዚያ 12 ቀን 2011 ዓ.ምበደሴ ከተማ በተካሄደው ሦስተኛው ዙር ብሔራዊ የክለቦች የቦክስ ውድድር ማራቶን ስፖርት ቡድን በወንዶች አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ።
ድሬዳዋና ፌደራል ፖሊስ ደግሞ በሁለት ወርቅና በሁለት ብር 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በመጪው ነሐሴ ወር 2011 ዓ.ም በሞሮኮ ለሚካሄደው 12ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን የሚወክሉ 20 ስፖርተኞች ባሳዩት ብቃት መሰረት በኮምቴ እንደሚመርጡም አመልክተዋል።
በአጠቃላይ ሴቶች ደግሞ አዲስ አበባ ከተማ የበላይነትን አግኝቷል፡፡
ከሚዚያ 9 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በደሴ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ሦስተኛው ዙር የክለቦች የቦከስ ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡
በውድድሩ በሁለቱም ጾታዎች ከ10 ክለቦች የተወጣጡ 70 ስፖርተኞች ተሳትፈዋል።
ተሳታፊ ስፖርተኞች በወንዶች ከ49 እስከ 91 ኪሎ ግራም፤ በሴቶች ደግሞ ከ48 እስከ 60 ኪሎ ግራም ክብደት ያላቸው ናቸው፡፡
ማራቶን ስፖርት በአጠቃላይ ውድድር ሦስት ወርቅ፣ አንድ ብርና ሁለት ነሐስ አምጥቶ በ13 ነጥብ በወንዶች አንደኛ ደረጃን ሲያገኝ፤ ፌደራል ማረሚያ ቤቶች ሁለት ወርቅ፣ ሁለት ብርና አንድ ነሐስ በማምጣት በ11 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።
ድሬዳዋና ፌደራል ፖሊስ ደግሞ በሁለት ወርቅና በሁለት ብር 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።
በተመሳሳይ በአጠቃላይ ድምር በሴቶች አዲስ አበባ፣ ደሴ ከተማና ድሬዳዋ በቅደም ተከተል ከአንድ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ አግኝተዋል።
የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጳውሎስ ማዳ እንዳሉት በውድድሩ ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ የቦክስ ስፖርተኞች ተሳትፈዋል፡፡
በመጪው ነሐሴ ወር 2011 ዓ.ም በሞሮኮ ለሚካሄደው 12ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን የሚወክሉ 20 ስፖርተኞች ባሳዩት ብቃት መሰረት በኮምቴ እንደሚመርጡም አመልክተዋል።
ውድድሩ የቦክስ ስፖርት ክለቦችን የእርስ በእርስ ግንኙነት ማጠናከር ዓላማው ማድረጉንም ተናግረዋል።
አቶ ጳውሎስ እንዳሉት በአራቱም ብሔራዊ የቦክስ ውድድሮች የተሻለ ውጤት ያስመዘገበው የዓመቱ የብሔራዊ የቦክስ ክለቦች አጠቃላይ አሸናፊ ይሆናል።
የማራቶን ቦክስ ክለብ ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር እዮብ ተስፋዬ በበኩላቸው ለውድድሩ ያደረጉት ቅድመ ዘግጅት በወንዶች አጠቃላይ አሸናፊ ለመሆን እንዳበቃቸው ተናግረዋል።
በ60፣ 64 እና 73 ኪሎ ግራም 3 ወርቅ ማምጣታቸዉን የተናገሩት ኢንስትራክተር እዮብ "በቀጣይም ቡድኑን በማጠናከር የተሻለ ውጤት ለማምጣት እንሰራለን" ብለዋል፡፡
ከተሳታፊዎች መካከል ወጣት ገነት ፀጋዬ አዲስ አበባን ወክላ በ52 ኪሎ ግራም ወርቅ ማምጣቷን ተናግራለች፡፡
በቀጣይ በሞሮኮ ለሚካሄደዉ ውድድርም ኢትዮጵያን ወክላ ወርቅ ለማምጣት ከወዲሁ ቅደም ዝግጅት እንደምታደርግ ተናግራለች፡፡
በቦክስ ስፖርት ለሰባት ዓመት መቆየቷን የተናገረችው ወጣት ገነት በወላይታ ከተማ በተደረገው ሁለተኛው ዙር የቦክስ ውድድር ወርቅ ማምጣቷን አስታውሳለች፡፡
በጥር ወር 2011 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በተካሄደው ሁለተኛው ዙር ብሔራዊ የቦክስ ክለቦች ውድድር በወንዶች ፌዴራል ፖሊስ፣ በሴቶች ደግሞ አዲስ አበባ ፖሊስ አሸናፊ መሆናቸው ይታወሳል ።