በኢትዮጵያ በአንድ አመት የታየው ለውጥ በመፅሃፍ ተሰንዶ ሊቀርብ ነው

57

አዲስ አበባ ሚያዝያ 11/2011 በኢትዮጵያ  በአንድ ዓመት ጊዜ ዉስጥ የተከናወኑትን ሁለንተናዊ ለውጦች የሚያመላክት መረጃ በመፅሃፍ ተሰንዶ ሊቀርብ ነው።

በዚሁ ዙሪያ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስተባባሪነት የተዘጋጀ የሁለት ቀንናት የምሁራን የውይይት መድረክ ዛሬ ተጀምሯል።

የመድረኩ ዋነኛ አላማ ለሚዘጋጀው መፅሃፍ ግባት ለማሰባሰብ ያለመ ሲሆን፤ በተለያዩ ዘርፎች ምርምር ያደረጉ ኢትዮጵያን እና የውጭ ሀገራት ምሁራን ተሳትፈውበታል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ዓመት የተመዘገቡ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ለውጦች ላይ ጥልቅ ትንታኔ እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም