ኢትዮጵያ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችላትን ስምምነት ከሩስያ ጋር ተፈራረመች

98

ሚያዚያ 8/2011 በሩስያ በተካሄደው 11ኛው አቶም-ኤክስፖ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር  ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ እና የሩስያ ስቴት አቶሚክ ኢነርጂ ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር ጀነራል አሌክሲ ሌካቼቭ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል የትግበራ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የትግበራ ፍኖተ ካርታ ስምምነቱ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን በግብርና፤ የህክምናውን ዘርፍ ለማዘመን፤ ለማምረቻው ዘርፍ ግብዓት እና ለመሳሰሉት ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል ነው፡፡

በተለይ በአለም እያደገ የመጣውን የህክምና ዘርፍ በኢትዮጵያ ለማዘመንና የቀዶ ጥገና ህክምናን የተቀላጠፈ ለማድረግ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ ለማዋል እንደሚሰራ ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ  ተናግረዋል፡፡
 

ትልልቅ ኢንደስትሪዎችን ለመገንባት በዝናብ ላይ ጥገኛ ከሆነ የሃይል ማመንጫ ኢትዮጵያ መላቀቅ አለባት ያሉት ሚኒስትሩ ፊታችንን ወደ ድብልቅ ኢነርጂ እናዞራለን ብለዋል፡፡

ምንጭ፡የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም