ዶክተር ጌታቸው ድንቁ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ - ኢዜአ አማርኛ
ዶክተር ጌታቸው ድንቁ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ ሚያዚያ 4/2011 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን መምህር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ።
ዶክተር ጌታቸው ከሚያዝያ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ስራውቸውን በይፋ መጀመራቸው ታውቋል።
አዲሱ የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሰልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ በአሁኑ ሰዓት በአዳማ ከተማ በአገር ዓቀፍ የሚዲያ ፖሊሲና የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ስትራቴጂ ረቂቅ ሰነዶች ላይ ውይይት እየመሩ ነው።
ዶክተር ጌታቸው ከመምህርነታቸው በተጨማሪ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃንን የተመለከቱ የተለያዩ ጥናቶች በማቅረብና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት ላይ የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ከፍተኛ ልምድ ማካበታቸው ይታወቃል።
የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንን ከግንቦት 2010 እስከ መጋቢት 2011 መጨረሻ አቶ ሰለሞን ተስፋዬ በዳይሬክተርነት ሲመሩት መቆየታቸው ይታወሳል።