የውሃ ነክ ተግባራትን የውሃ መጠቀሚያ ታሪፍ የሚወስን ደንብ ተዘጋጀ - ኢዜአ አማርኛ
የውሃ ነክ ተግባራትን የውሃ መጠቀሚያ ታሪፍ የሚወስን ደንብ ተዘጋጀ
አዲስ አበባ ሚያዝያ 3/2011 መስኖን ጨምሮ የሌሎች ውሃ ነክ ተግባራትን የውሃ መጠቀሚያ ታሪፍ የሚወስን ረቂቅ ደንብ ተዘጋጀ።
የኢትዮጵያ የተፋሰስ ልማት ከፍተኛ ምክር ቤት ረቂቅ ደንቡን በሚመለከት ውይይት እያደረገ ነው።
የተፋሰሶች ልማት ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ግዛው እንደገለጹት፣ ባለስልጣኑ የውሃ መጠቀሚያ ታሪፍን ለመወሰን ረዥም ጊዜ የወሰደ ጥናት አካሄዷል።
የመስኖ ልማት፣ አሳ ማስገር፣ የውሃ ኃይል ማመንጨት፣ ማዘጋጃ ቤታዊ የውሃ አቅርቦትና ከውሃ ሃብት ጋር የተያያዙ መዝናኛዎች ታሪፍ የወጣላቸው ዘርፎች መሆናቸውን አብራርተዋል።
በነዚህ ዘርፎች የተሰማሩ አካላት ከሚያገኙት ከሁለት እስከ ሶስት በመቶ የሚሆነውን ለተጠቀሙበት የውሃ ታሪፍ የሚከፍሉ ይሆናል ነው ያሉት።
ረቂቅ ደንቡ በውይይት ከዳበረ በኋላ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።