ቀጥታ፡

የሲዳማ ሴቶች በሀዋሳ ሰልፍ እያካሄዱ ነው

ሀዋሳ ሚያዝያ 1/2011 የሲዳማ የክልልነት ጥያቄን የተመለከተ በብሄሩ ተወላጅ ሴቶች የተጠራ ሰልፍ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው ።

ማለዳ 12 ሰዓት በጀመረው ሰልፍ ከሁሉም የሲዳማ ዞን ወረዳዎችና ከተሞች የተወጣጡ ወጣት ሴቶችና እናቶች ተሳትፈውበታል ።

ከወልደአማኑኤል ዱባለ አደባባይ የተነሳው ሰልፉ መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ ነው ።

ሰልፈኞቹ የሕዝብ ውሳኔ ቀን ተቆርጦ ይነገረን፣ጥያቄያችን ሕገ-መንግስታዊ ትግላችንም ሰላማዊ ነው፣ ጥያቄያችን በሕገ-በመንግስቱ መሰረት ብቻ ይመለስ፣ ፍትህ ለሲዳማ ሕዝብ የሚሉ መልእክቶችን አስተላልፈዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም