መቀሌ 70 እንደርታ ወላይታ ዲቻን አንድ ለባዶ አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
መቀሌ 70 እንደርታ ወላይታ ዲቻን አንድ ለባዶ አሸነፈ
መቀሌ መጋቢት 29/2011 በመቀሌ ትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲዬም በተካሄደው 19ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ ወላይታ ዲቻን አንድ ለባዶ አሸንፏል።
መቀሌ 70 እንደርታ ዛሬ የተካሄደውን ግጥሚያ ያሸነፈው በ73ኛው ደቂቃ ላይ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት በአማኑኤል ገብረ ሚካኤል አማካኝነት ግብ በማስቆጠሩ ነው።
የመቀሌ 70 እንደርታ ክለብ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ወደ 42 በማሳደግ የሊጉ መሪነቱን አጠናክሯል።
ከጨዋታው በዋላ የወላይታ ዲቻ ተጫዋቾች በታክቲክና ተደጋጋሚ የግብ ሙከራዎች በማድረግ በጨዋታ ብልጫ ማሳየታቸውን የክለቡ አምበል ደጉ ደበበ ተናግሯል ።
የመቀሌ 70 እንደርታ ክለብ አምበል ሚካኤል ደስታ በበኩሉ ክለባቸው የተጠበቀውን ያህል ጨዋታ አለማሳየታቸውን ገልጿል።
በዛሬው ጨዋታ የታዩ ክፍተቶችን በቀጣይ ጨዋታዎች ለማስተካከል ጥረት እናደርጋለን ብሏል።