ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለሥራ ጉብኝት ባህር ዳር ገቡ

123

ባህር ዳር መጋቢት 26/2011 የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለሥራ ጉብኝት ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ባህር ዳር ከተማ ገቡ።

ፕሬዚዳንቷ ባህር ዳር ከተማ ሲደርሱ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንንና ሌሎች የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንቷ በቆይታቸው በባህር ዳር ፈለገ ሕይወት ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባውን የኦክሲጂን ማምርቻ ማዕከል መርቀው ሥራ ያስጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የባህር ዳር ሐምሊን ፌስቱላ ማዕከልንና የባህር ዳር ፈለገ ሕይወት ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታልን የጤና አገልግልት አሰጣጠን ይጎበኛሉ።

አዲሱን የባህር ድር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ጊዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሥራ እንቅስቃሴንም እንደሚጎበኙም ታውቋል።

ከእዚህ በተጨማሪ ፕሬዚዳንቷ ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከተውጣጡ ምሁራን ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም