ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መቱ ከተማ ገቡ

መቱ መጋቢት 26/2011 የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር  ዶክተር  አብይ አህመድ ዛሬ መቱ ከተማ ገቡ፡፡

ጠቅላይ ሚንስትሩ መቱ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን በቆይታቸው ከኢሉአባቦር ዞን ነዋሪዎች ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በመቱ ከተማ ለሚያስገነባው ዘመናዊ የግብይት ማዕከልም የመሰረተ ድንጋይ እንደሚያስቀምጡም ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም