ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ጅግጅጋ ገብተዋል

177

ጅግጅጋ መጋቢት 25/2011 የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ጅግጅጋ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሐመድና የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ሶዴፓ)ሊቀመንበር አቶ አህመድ ሺዴ ከክልሉ ካቢኔ አባላት ጋር በመሆን ተቀብለዋቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በሶዴፓ 10ኛ ጉባዔ ማጠቃለያ ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም