በአቡና ግንደበረት ወረዳ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ተገልብጦ የሰው ህይወት አለፈ

66

አምቦ መጋቢት 23/2011 በምዕራብ ሸዋ ዞን ከግንደበረት ወደ ጊንጪ በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ተገልብጦ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በአቡና ግንደበረት ወረዳ ፖሊስ መምሪያ  የትራፊክ ክፍል ኃላፊ ኮማንደር ታደሰ አመዩ እንደገለጹት አደጋው የደረሰው  የታርጋ ቁጥሩ ኮድ 3- 64307 ኦሮ የሆነው ህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ  ዛሬ ጥዋት 12 ሰዓት ተኩል አካባቢ በወረዳው  ሀሮ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሙጠማ በተባለው ስፍራ በመገልበጡ ነው።

አውቶብሱ 61 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ እንደነበረ አስታውሰው በአደጋው ህይወታቸው ካለፈው ሌላ 51 ሰዎች   ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በጊንጪ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሽከርካሪው ለጊዜው መሰወሩን  ያመለከቱት  ኮማንደር ታደሰ  የአደጋው መንስኤ  እየተጣራ እንደሚገኝ  ጠቁመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም