ቀጥታ፡

የዛሬ የፕሪሚየር ሊግ 4 ጨዋታዎች በተመሳሳይ ውጤት ተጠናቀቁ

መጋቢት 22/2011 በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 18ኛ ሳምንት ጨዋታ ጅማ አባ ጅፋርና ኢትዮጵያ ቡና ተጋጣሚዎቻቸውን በተመሳሳይ ውጤት አንድ ለባዶ አሸነፉ።

ፋሲል ከነማና ወላይታ ድቻም ተጋጣሚዎቻቸውን መቀሌ ሰባ እንደርታንና ሃዋሳ ከነማን አንድ ለባዶ ማሸነፍ ችለዋል።

በጅማ ከተማ በተካሔደው ጨዋታ ባለሜዳው ጅማ አባጅፋር ቅድስ ጊዮርጊስን ያሸነፈው ጨዋታው በተጀመረ በ10ኛው ደቂቃ ማማዱ ሲዲቤ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል ነው። 

ጅማ አባጅፋር ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ከ25 ወደ 28 ያሳደገ ሲሆን ደረጃውንም ከ7ኛ ወደ ስድስተኛ ከፍ ማድረግ ችሏል፡፡

ተጋጣሚው ቅዱስ ጎርጊስም በመሸነፉ ምክንያት በያዘው 29 ነጥብ ከሶስተኛ ወደ አራተኛ ደረጃ ተንሸራቷል።

መቀሌ ላይ በተካሔደው የኢትዮጵያ ቡና እና የውልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ግጥሚያ ደግሞ የቡናው አማኑኤል ዮሃንስ በ51ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ክለቡን አሸናፊ አድርጓል።

የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተጨዋቾች ግብ ሊሆን የሚችል አንድ የፍፁም ቅጣት ምት እድል በ19ኛው ደቂቃ ላይ ቢያገኙም ሳጠቀሙበት ቀርተዋል።

በተያያዘ ዜና ጎንደር ላይ መቀሌ ሰባ እንደርታን የገጠመው ፋሲል ከነማ በአለምብርሃን ይግዛው አማካኝነት በ75ኛው ደቂቃ በተገኘች ጎል አሸናፊ ሲሆን ወላይታ ሶዶ ላይ በተደረገ ጨዋታ ደግሞ ባለሜዳው ወላይታ ድቻ ሃዋሳ ከነማን በ21 ቁጥሩ እሸቱ መና ብቸኛ ግብ ማነፍ ችሏል  ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም