ከመጋቢት እስከ መጋቢት የፎቶ ዐወደ ርዕይ ተከፈተ - ኢዜአ አማርኛ
ከመጋቢት እስከ መጋቢት የፎቶ ዐወደ ርዕይ ተከፈተ
አዲስ አበባ መጋቢት 22/2011 የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድን የአንድ ዓመት ጉዞን የሚያሳይ የፎቶ ዐውደ ርዕይ ተከፈተ::
ዐውደ ርዕዩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መጋቢት 24 ቀን 2010ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ከተሰየሙ አንስቶ በ365 ቀናት ያደረጉትን ሁነቶች የሚያሳይ ነው።
በባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው ዛሬ ጠዋት በሚሊኒየም አዳራሽ የተከፈተው ዐውደ ርዕዩ እንደ አንድ ትዝታን መዝግቦ ለታሪክ እንደማስቀምጥ የሚታይ መሆኑም ተገልፀዋል::
ይህ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተዘጋጀው የፎቶ ዐውደ ርእይ ከ250 በላይ የታተሙና ዲጂታል ፎቶግራፎችን ያካተተ ሲሆን ባለፈው አንድ ዓመት የነበረውን የጠቅላይ ሚኒስትሩንና የሌሎች ኃላፊዎችን እንቅስቃሴና የሕዝብንም ምላሽ ያካተተ ነው::
የፎቶ ዐውደ ርእዩ ከፎቶግራፎቹ በተጨማሪ በጥበብ አደራጅ ኤዶም በለጠ የተሠራ የዛፍ አንቲክ ጥበብን ይዟል::
ይህ የዛፍ አንቲክ ጥበብ በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ የበዓለ ሢመት ንግግር ላይ የተመሠረተና ኢትዮጵያዊነትን የሚያንፀባርቅ እንደሆነም ተገልጿል::
'ከመጋቢት እስከ መጋቢት' የተባለው ይኸው ዐውደ ርዕይ በሚሊኒየም አዳራሽ ከመጋቢት 22 እስከ 27 የሚቆይ ይሆናል።