ዴንማርክ ለቀጣዩ የኢትዮጵያ ምርጫ የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች

63

አዲስ አበባ መጋቢት 19/2011 ዴንማርክ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲን ለማጠናከር ለቀጣዩ ምርጫ የሚውል የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን  ዶላር ድጋፍ አደረገች።

በተመሳሳይ በኢትዮጵያ የሴቶችን እኩልነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ 3 ሚሊዮን 29 ሺህ ዶላር ድጋፍ አድርጋለች።

የመጀመሪያው የድጋፍ ሥምምነት በዴንማርክ የልማት ኮርፖሬሽን ሚኒስትር ዩላ ቶርናስና በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የልማት መርኃ ግብር ተፈርሟል። 

ሁለተኛው የድጋፍ ሥምምነት ደግሞ በዴንማርክ የልማት ኮርፖሬሽን ሚኒስትር ዩላ ቶርናስ በተመድ የሴቶች ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ በሌቲይ ቼዋራ ተፈርሟል።

ሚኒስትሯ ዩላ ቶርናስ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፤ ለምርጫ የተደረገው ድጋፍ በኢትዮጵያ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድ የሚሰሩ ሥራዎችን ያግዛል።

ድጋፉ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተሰጠውን ኃላፊነትና ተግባራት በአግባቡ እንዲወጣና ምርጫው በኅብረተሰቡ ዘንድ ተዓማኒነት እንዲኖረው ለማድረግ እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።

ከምርጫ ጋር የተያያዙ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አጠቃቀምንና ከምርጫ ጋር ተያይዘው የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት እንዲሁ ድጋፍ እንደሚደረግ ተገልጿል።

በተመሳሳይ ለሴቶች እኩልነትና ተጠቃሚነትም የተደረገው ድጋፍ በአገሪቱ ብሔራዊ እቅድ ጋር ተጣጥሞ የሚሰሩ ሴቶችን መሰረት ያደረጉ ሥራዎችን ለመደፍ እንደሚውል ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም