የሳውዝዌስት አየር መንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን በሞተር ብልሽት በረራውን አቋረጠ

78

አዲስ አበባ መጋቢት 18/2011 ንብረትነቱ የሳውዝዌስት አየር መንገድ የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ባጋጠመው የሞተር ብልሽት ምክንያት በረራውን አቋረጠ።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ በደረሰው አደጋ ምክንያት ከበረራ የታገደው ይህ ቦይንግ 737 አውሮፕላን ያለተሳፋሪ በአብራሪዎች እንዲበር ተፈቅዶለት ጉዞ በጀመረ በአስር ደቂቃ ውስጥ የአውሮፕላኑ አንደኛው ሞተር ከልክ በላይ በመሞቁ ምክንያት ወደ ካሊፎርኒያ ያደርግ የነበረውን በረራ አቋርጦ ኦርላንዶ ውስጥ በድንገት ለማረፍ ተገዷል ሲል ሲኤንቢሲ ከደቂቃዎች በፊት ዘግቧል ።

ሰሞኑን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የደረሰውን አደጋ ከማሰልጠኛ ሲሙሌተርና አውሮፕላኑን ያበር ከነበረው ፓይለት ጋር የተያያዘ እንደሆነ በአንዳንድ የውጭ ሚዲያዎች አማካኝነት ዘገባ መሰራቱ ይታወሳል።

ይሁንና ቦይንግ 737 ማክስ 8 አይሮፕላኖች ከአብራሪዎቹ ሳይሆን የራሱ የአይሮፕላኑ የቴክኒክ ችግር በድጋሚ መፈተሽ እንዳለበት ዘገባዎች ያሳያሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም