የካናዳ ኤምባሲ በአውሮፕላኑ አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች የመታሰቢያ መርሐ ግብር አካሄደ

120

አዲስ አበባ መጋቢት 17/2011 በኢትዮጵያ የካናዳ ኤምባሲ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች የመታሰቢያ መርሐ ግብር አካሄደ።

ዛሬ በኤምባሲው ቅጥር ግቢ በተካሄደው የመታሰቢያ መርሐ ግብሩ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችና ተወካዮች ተገኝተዋል።

በአደጋው ምክንያት ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ያጡ የሟች ቤተሰቦችም በመርሐ ግብሩ የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር አንቶኒዮ ቼቭሪር ለሟች ቤተሰቦችና ዘመዶች ልባዊ መጽናናትን ተመኝተዋል። 

በተመሳሳይም በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ምክትል ቋሚ ተወካይ ማህሌት ኃይሉ ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል። 

መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲጓዝ በምስራቅ ሸዋ ዞን ጊምቢቹ ወረዳ በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን የ35 አገራት 149 ዜጎች እና 8 የአውሮፕላኑ ሰራተኞች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም