ከደመወዛቸው 80 በመቶውን ለተማሪዎቻቸው የሚደግፉት ኬንያዊ መምህር የ1 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አሸነፉ

90

መጋቢት 16/2011 ከወርሃዊ ደመወዛቸው አብዛኛውን ለድሃ ተማሪዎች ድጋፍ የሚያውሉት ኬንያዊው የሳይንስ መምህር ፒተር ታቢቺ የዓለም ምርጥ መምህር በመባል የ1 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አሸንፈዋል።

በኬንያ ጠረፋማ መንደር ፐውኒ ጥቂት መጻህፍት እና በተማሪዎች የተጨናነቁ የመማሪያ ክፍሎች ባሉበት ትምህርት ቤት እያስተማሩ ስኬታማ ሆነዋል።

መምህሩ ተማሪዎቻቸው የነገ ህይወታቸው በሳይንስ ላይ የተመሰረተ እንዲሆንም ይመኛሉ።

ዱባይ ውስጥ በተካሄደ ስነስርዓት ሽልማታቸውን የተቀበሉት ፔተር በስምጥ ሸለቆ አካባቢ በሚገኝ የጠረፍ መንደር ባለ ትምህርት ቤት ብዙ ስኬት ማስመዝገባቸው ተነግሯል።

መምህር ፒተር 80% ደመወዛቸውን የደንብ ልብስና መጻህፍት መግዛት ለማይችሉ ተማሪዎቻቸው ድጋፍ ያደርጋሉ።

በፕዋኒ መንደር በሚገኘው ሚክስድ ዳይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከሚማሩ ተማሪዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ ድሃዎች፣ ወላጅ የሌላቸው ናቸው።

ምንጭ፦ቢቢሲ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም