ኮሚቴው ባንኩ ለተፈናቃዮች የለገሰውን 4 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አልቀበልም አለ

64

ባህር ዳር መጋቢት 15/2011 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለአማራ ክልል ተፈናቃዮች የለገሰውን  4 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንደማይቀበለው የክልሉ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡

የኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አገኘው ተሻገር ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት ኮሚቴው ድጋፉን የማይቀበለው የክልሉ ተፈናቃዮች ያሉበትን ሁኔታ ያማከለ ባለመሆኑ ነው።

ባንኩ ለተፈናቃዮች ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

ኮሚቴው በቅርቡ በአዲስ አበባ በክልል ፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ በተደረገ እንቅስቃሴም ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ መሰባሰቡንና ቃል ማስገባቱን ተናግረዋል።

በክልሉና ከክልሉ ውጭ የተፈናቀሉ ከ90 ሺህ በላይ ተፈናቃዮችን ለማቋቋም የሚያስፈልገውን አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር እያሰባሰበ እየተከናወነ መሆኑን  ገልጸው ፤ቃል የገቡ ሰዎች ገንዘቡን ገቢ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመላው አገሪቱ ለተፈናቀሉ ወገኖች 100 ሚሊዮን ብር ለመለገስ በዚህ ሳምንት መወሰኑ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም