መንግስት የፖለቲካውን ያህል ለኢኮኖሚው ትኩረት መስጠት አለበት ተባለ

86

አዲስ አበባ መጋቢት 14/2011 መንግስት ለፖለቲካው የሰጠውን ትኩረት ያህል ለኢኮኖሚውም መስጠት እንዳለበት ተጠቆመ።

በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት አዘጋጅነት 'አዲስ ወግ' በሚል ርዕስ እየተካሄደ ያለው አገራዊ ምክክር ዛሬም ቀጥሎ ውሏል።

በመድረኩ ከሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ግለሰቦች እየተሳተፉበ ይገኛሉ።

በዛሬው መርሃ-ግብርም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚና የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያተኮሩ መነሻ ሃሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ለውይይት መነሻ ሃሳቦችን ያቀረቡት የማክሮ ኢኮኖሚ ተመራማሪና መምህር ዶክተር ሰኢድ ኑሩ፣ የመሬት ስሪት ተመራማሪና የጥናት ባለሙያ አቶ ደሳለኝ ራህመቶ፣ የህብረት ባንክ የቦርድ ሊቀ-መንበርና የፋይናንስ ዘርፍ ባለሙያው አቶ ዛፉ ኢየሱስወርቅ እና ወይዘሮ ብርሃኔ አሰፋ ናቸው።

አቅራቢዎቹ እንዳሉት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ በፖለቲካው ዘርፍ በርካታ ለውጦች ተካሂደዋል።

ይሄን በፖለቲካ የተገኘውን ለውጥ በኢኮኖሚ በመድገም የገጠሩን ማህበረሰብ ኑሮ ለማሻሻልም መሰራት ይገባዋል ሲሉ ነው ያብራሩት።

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ተጨባጭ ወቅታዊ ሁኔታ በኢኮኖሚው ዘርፍ በግልፅ የት መድረስ እንዳለበት በማህበረሰቡ መግባባት መፈጠር አለበትም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም