የአርመንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በኢትዮጵያና ሩዋንዳ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

90

አዲስ አበባ መጋቢት 11/2011 የአርመንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዞሃራብ ማንታስካንያን በሚያዚያ ወር መግቢያ ላይ ኢትዮጵያንና ሩዋንዳን እንደሚጎበኙ ተገለጸ።

የአርማኒያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አና ናግሀድአልያን እንደገለጹት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በሩዋንዳ ጉብኝታቸው የዘር ማጥፋት የተፈጸመበትን 25ኛ ዓመት ለመዘከር በሚደረገው ዝግጅት ላይ ይገኛሉ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በአገራቱ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚያግዝ  አርካ የተሰኘው የአገሪቱ ዜና አገልገሎት ዘግቧል።

የቀድሞዋ ሶቪዬት ህብረት አካል የነበረችው አርመኒያ በምእራብ እስያና በምስራቅ አውሮፓ መካከል የምትገኝ ትንሽ አገር ስትሆን ሶሰት ሚሊዮን የማይሞላ ህዝብ ይኖርባታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም