ቀጥታ፡

ኢትዮጵያና ኬንያ "በትብብርና ስኬት ዘመን ላይ ማተኮር ይገባቸዋል" - ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ

አዲስ አበባ  መጋቢት 9/2011 በኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ በደረሰው አደጋ  ምክንያት በኬንያም የሀዘን ቀን ታስቦ ውሏል፡፡

ኬንያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ጋር ናይሮቢ በሚገኙ የተለያዩ ቤተ-እምነቶች  ባዘጋጀው ስርዓተ ፀሎት ላይ ፕሬዝዳንት   ኡሁሩ ኬንያታ  በተወካያቸው  የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምክትል አምባሳደር ማቻሪያ ካማው አማካኝነት  መልዕከት አስላልፈዋል፡፡

"የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኬንያውያንም ኩራት ነው" ያሉት ፕሬዚደንት ኡሁሩ፤ ሁለቱ ሀገራት ለወደፊቱም "በትብብርና ስኬት ዘመን ላይ ማተኮር ይገባቸዋል" ማለታቸውን ተወካያቸው ተናግረዋል።

በኬንያ የኢፌዲሪ ቋሚ ተጠሪና አምባሳደር መለስ ዓለም በበኩላቸው በእንደዚህ ዓይነቱ መሪር የሀዘን ወቅት "የሌላውን ወገን ሃዘን መጋራትና በችግሩ ወቅት ከጎኑ መቆም ዘመን ተሻጋሪና አኩሪ ኢትዮጵያዊ ባህላችን ነው" ብላዋል።

ኤምባሲው ሊኖረው ስለሚገባው ግንኙነት የጠቀሱት አምባሳደር መለስ "አንዳንድ ወገኖች የሀገር ጉዳይ በኤምባሲ ብቻ የሚሰራ ሥራ ቢመስላቸውም፤ የኤምባሲው አብይ ተልዕኮ የዜጎችን አቅም የማስተባበር ሥራ ነው፤ "ሁሉም በአገሩ ጉዳይ አምባሳደር ነው" ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም