ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የጌዴኦ ተፈናቃዮችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ  መጋቢት 8/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር  አብይ አህመድ በጌዴኦ ዞን ገደብ ወረዳ የሚገኙ ተፈናቃዮችን እየጎበኙ ነው።

የሠላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል በዞኑ የተጠለሉ ዜጎችን ወቅታዊ ሁኔታ ለማየት ተመሳሳይ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተፈናቃዮችን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው፤ የጌዲኦ ተፈናቃዮችን መንግሥት ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመሆን እርዳታ በማቅረብ እየደገፈ ይገኛል።   

በስፍራው በፊት ከነበረው ተረጂ በተጨማሪ 100 ሺህ እርዳታ ፈላጊ ተፈናቃዮች እንደሚገኙም ለማወቅ ተችሏል። 

https://www.youtube.com/watch?v=7ag-eEXNMjY&t=2s

የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል የጌዲኦ ተፈናቃዮችን አስመልክተው የሰጡት መግለጫ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም