የትግራይ ክልላዊ መንግስት በጌዴኦ ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች አምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ

110

መቀሌ መጋቢት 7/2011 የትግራይ  ብሔራዊ ክልላዊ  መንግስት በደቡብ ክልል ጌዴኦ ዞን ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች  አምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ወሰነ፡፡ 

የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ  ሊያ ካሳ ማምሻውን እንደገለጹት የክልሉ መንግስት ለእነዚህ  ወገኖች ድጋፍ እንዲውል የወሰነው ገንዘብ   በተጣበበ የበጀት እጥረት ውስጥ ሆኖ ነው፡፡

የክልሉ መንግስት በተጨማሪም 15 ሐኪሞች የሚገኙባቸው 25 የጤና ባለሙያዎች ቦታው ድረስ ሄደው ነጻ የህክምና እርዳታ እንዲያደርጉም  ወስኗል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም