ክለቡ የደጋፊዎች ማህበሩን በአዲስ መልክ መሰረተ - ኢዜአ አማርኛ
ክለቡ የደጋፊዎች ማህበሩን በአዲስ መልክ መሰረተ
ጅማ መጋቢት 7/2011 የጅማ አባጅፋር እግር ኳስ ክለብ የደጋፊዎች ማህበር በአዲስ መልክ ተመሰረተ፡፡
የጅማ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አጀኢብ አባመጫ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት ማህበሩ የክለቡን ውጤታማነት የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት፡፡
ማህበሩ ለክለቡ ወገንተኛና ተጋጣሚዎቹን ደግሞ ያለ አድልኦ የሚያስተናግድ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።
ጠንካራ መዋቅር ያለው ማህበር ለክለቡ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የጅማ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህር ዶክተር ወንድምአገኝ ደምሴ ናቸው።
ማህበሩ መዋቀሩንና አደረጃጀት ማጎልበት እንዳለበትም አመልክተዋል።
ክለብ በችሎታው ውጤት አስመዝግቦ እንዲወጣ ማድረግ የደጋፊዎች ሚና መሆን እንዳለበትም ዶክተር ወንድምአገኝ አሳስበዋል።
የደጋፊዎች ድጋፍና ተቃውሞ ሰላማዊ ፣ህጋዊና ምክንያታዊ እንዲሆን መስራት እንደሚጠበቅበትም ጠቁመዋል።
የማህበሩ የሥራ ድርሻ ከክለቡ አመራሮች ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ለደጋፊዎች ይፋ ይሆናል ብለዋል።
ጅማ ኣባጅፋር የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የ2010 ሻምፒዮን ነበር።