ኢትዮጵያ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች በአየር ክልሏ እንዳይበሩ አገደች

72

አዲስ አበባ መጋቢት 5/2011  ኢትዮጵያ ቦይንግ 737 ማክስ 8 እና 9 አውሮፕላኖች በአየር ክልሏ እንዳይበሩ አገደች።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አንሙት ለማ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ባለስልጣኑ ከዛሬ ጀምሮ አውሮፕላኖቹ በአገሪቷ የአየር ክልል እንዳይበሩ ከልክሏል።

በተመሳሳይ አሜሪካ በዛሬው ዕለት ሁሉም የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከበረራ አገልግሎት እንዲወጡ ማገዷን አስታውቃለች።

ከሰሞኑ ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ይበር የነበረ የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ተከስክሶ 157 ሰዎች ህይወታቸውን በማጣታቸው በርካታ አገሮች አውሮፕላኑ ላይ እገዳ ጥለዋል።

ከ40 በላይ አገሮች አየር መንገዶች ምርመራው እስኪጣራ ለጊዜው ቦይንግ 737 ማክስ 8 እና 9 አውሮፕላንን ያገዱ ሲሆን፤ የአውሮፓ ህብረትም በአህጉሪቷ የአየር ክልል እንዳይበር ጭምር ከልክሏል።

https://www.youtube.com/watch?v=pKEX_F5ao3w

ሳቅ በእንባ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም