ቀዳማዊት እመቤት በዱብቲ ወረዳ ለሚገነባ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ

69

ሰመራ መጋቢት 5/2011 ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ ለሚገነባ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጡ። 

ቀዳማዊት እመቤቷ በክልሎች የትምህርት ተደራሽነትን ለማገዝ በያዙት ዕቅድ መሰረት የመሰረት ድንጋዩን ማስቀመጣቸው ተገልጿል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጠሃ አህመድ " ወረዳው ከፍተኛ የተማሪዎች ቁጥር ያለበት በመሆኑ የሚገነባው ትምህርት ቤት መጨናነቅን በማስቀረት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ አስተዋጾ ይኖረዋል" ብለዋል።

የትምህርት ቤቱ ግንባታ 20 ሚሊዮን ብር እንደሚፈጅ ኃላፊው ተናግረዋል ።

በትላንትናው እለት በተካሄደው የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ስነ- ስርአቱ ላይ የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም