የአውሮፓ ህብረት ቦይንግ 737 ማክስ ስምንት አውሮፕላን በአውሮፓ አየር ክልል እንዳይበር አገደ

58

መጋቢት 3 / 2011 የአውሮፓ ህብረት  ቦይንግ  737 ማክስ ስምንት አውሮፕላን   በአውሮፓ አየር ክልል እንዳይበር  ማገዱን  ይፋ አደረገ፡፡

ቦይንግ 737 ማክስ ስምንት አውሮፕላን  በአውሮፓ አየር ክልል እንዳይበር የታገደው  ለ157 ሰዎች ህልፈት ምክንያት የሆነው  በኢትዮጵያ በተከሰከሰው አውሮፕላን መነሻ በማድረግ  ነው፡፡

የአውሮፓ አቬየሽን ደህንነት ኤጄንሲ (EASA) በመግለጫው እንዳስታወቀው  በአውሮፓ የሚገኙ ሁሉም ቦይንግ 737 ማክስ ስምንት አውሮፕላን አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ ተደርጓል፡፡

በሌሎች በሶስተኛ ወገን በንግድ የሚንቀሳቀሰሱ ቦይንግ 737 ማክስ ስምንት አውሮፕላኖች በአየር ክልሉ ውስጥ በረራ እንዳይደረግም  አግዷል፡፡

የተከሰተውን አደጋ የማጣራት ሥራ እየተካሄደ ነው ያለው  ህብረቱ፤ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅም ግዜው  ገና ነው ብሏል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ  የኢንግሊዝ ሲቪል አቬየሽን ባለስልጣን፣ ቻይና ፣ ስንጋፖርና አውስትራሊያን  የመሳሰሉት ሀገራት ቦይንግ 737 ማክስ
ስምንት አውሮፕላን በአየር ክልላቸው እንዳይበር  ማገዳቸው ይታወሳል ሲል የዘ ኢንዲፐንዴንት ዘገባ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም